ልዩ ልዩ መልእክቶች

ነሐሴ 7 ቀን 2004 ዓ.ም  
‹‹ች››
ኢትዮጵያ ታደሰች ኑ ልጆቼ እያለች
የብሔር ብሔረሰቦች እናት ሆነች
በዘውድ ነገሰች ቅርሷን አነሳች
በጠቅላይ ሚንስቴር ትመራለች
በየአምስት ዓመቱ እያስመረጠች
ትሾማለች በውድድር ፓርላማ እያስገባች
በጠባይ መምራት ነው ሳንሰለች
የሕዝብን ፍቅር ማግኘት ነው አማለለች
ኢትዮጵያን እንደልድላት አስማረች
ብርቅዬ ነኝ የዓለም መክሊት ታደለች
በሰረገላቸው ሰልፎችዋ ትታያለች
ችቦው ይበራል ታድጋለች
ታሪክ ይጻፋል ወራለች
ለዓለም ሕዝብ ምሳሌ ትሆናለች
አፍሪካን አንድ አድርጋ ትመራለች
የአፍሪካ ልጆቼ ተደሰቱ እያለች
ዓለምን በሙሉ ታመጣለች ትስባለች፡፡

   የእግዚአብሔር ባርያና አገልጋይ
ሊቀ. ትጉ. ባሕ. ገ/መስቀል ኃ/መስቀል
              አዲስ አበባ



እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!







                         ነሐሴ 3 ቀን 2004 ዓ.ም
‹‹ኝ››
እሰይ የምስራች ሌሊቱ ነጋልኝ
የሰባ አራት ዓመት እዳ ተደመሰሰልኝ
እኔ እናታችሁ ኢትዮጵያ ነኝ
ቁሙ ካጠገቤ እልል በሉልኝ!!!
የትንሳኤው ብርሃን ዘመነ ማቴዎስ እሰይ ደረሰልኝ
ነገሩ ተዘጋ እሳቱ አለፈልኝ
እኔ ኢትዮጵያ ነኝ ልጆቼ ተሰባሰቡልኝ
የእባቡ መርዝ ከሸፈ ተደመሰሰልኝ
እርሻው አማረ ዘሩ ተዘራ ቡቃያው በቀለልኝ
ምነው እናንተ ካህናት አስቸገራችሁኝ
ተመለሱ ይበቃል እንክርዳድና ገለባ አትሁኑብኝ
ለእኔ ይበቃኛል ቅጥሩ ይፍረስልኝ
ከእንግዲህ መከራ አልፈልግም መሬቱ ይጥራልኝ
ድንግል ማርያም በእንባዋ ደረሰችልኝ
የእኔ መድኃኒዓለም ተመስገንልኝ
ቅዱሳን መላዕክት ተሰለፉልኝ
እናንተም ሰማዕታት አኮብኩቡልኝ
ተመስገን አምላኬ ተመስገንልኝ፡፡
(ት/ሚልክ. ም.1 ቁ.6) 

   የእግዚአብሔር ባርያና አገልጋይ
ሊቀ. ትጉ. ባሕ. ገ/መስቀል ኃ/መስቀል
              አዲስ አበባ



እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!


No comments:

Post a Comment