Tuesday 26 November 2013

Memehir G/meskel.....የ28 ዓመት መንፈሳዊ ጉዞ disc 5

http://www.youtube.com/watch?v=9ffawj99THQ



እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

Memehir G/meskel.....የ28 ዓመት መንፈሳዊ ጉዞ disc 8



http://www.youtube.com/watch?v=C3vDhDNR9qA

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

Sunday 29 September 2013

የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር የ28ተኛ ዓመት የወንጌል የምስረታ በዓሉን በታላቅ ድምቀት አከበረ


በወርሃ መስከረም በእለተ እሁድ የቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት ቀን ማለትም በ12/01/2006ዓ.ም የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር የ28ተኛ ዓመት የወንጌል የምስረታ በዓሉን በታላቅ ድምቀት አከበረ 

በእለቱ ፕሮግራሙን በጸሎት የከፈቱት  የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራችና የበላይ ጠባቂ እንዲሁም የጠቅላላ ጉባኤው አፈጉባኤ የሆኑት ሊቀ ትጉ.ባሕ ገ/መስቀል ኃ/መስቀል በአሉን አስመልክተው ንግግር ካደለጉ በኃላ ማህበሩ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ቀን ከለሊት ደፋ ቀና በማለት ለዚህ ላበቁት ለማህበሩ ደጋፊዎች መዕመናን ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል
 በመቀጠልም በዓሉን አስመልክተው ማኅበሩ ከዛሬ ጀምሮ በሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር ዘተዋህዶ በሚል በEBS TV ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 3፡30 እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ የሚተላለፍ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መጀመሩን ካበሰሩ በኃላ የ28ተኛ ዓመት የሚገልጽ ሻማ በመለኮስ ፕሮግራሙን በይፋ ከፍተዋል 



በመጨለሻም በአባታችን በሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ ኣባ ወልደማርቆስ  ቡራኬና ቃለምዕዳን ተሰጥቶ የዕለቱ ፕሮግራም ተፈፀመ
 


እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

Monday 10 September 2012

መልካም አዲስ ዓመት



በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

በመላው ዓለም ለምትገኙ ምእመናን በሙሉ እንኳን 2005 . አዲስ ዓመት
ለዘመነ ማቴዎስ በሠላም በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን እያልን የከበረ ሠላምታ
እናቀርብላችኃለን፡፡
  
    ከመንፈሳዊ ሠላምታችን በመቀጠል የምንገልፅላችሁ ነገር ቢኖር አዲሱ ዓመት
ዘመነ ማቴዎስ የሰላም ' የደስታ ' የፍቅር ' የአንድነትና የብልፅግና እንዲሆንልን
እየተመኘን ጉባኤያችን መስከረም 13 ቀን እሁድ 27ተኛውን ዓመት የምስረታ በዓሉን
በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ ሁላችሁም ይህንን በዓል ለማክበር
እንድትዘጋጁ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡


                         
                                           መልካም አዲስ ዓመት


                                               የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር
                                              መሥራችና የበላይ ጠባቂ እንዲሁም
                                             የጠቅላላ ጉባኤው ዋና ሰብሳቢ
                                             ሊቀ ትጉ.ባሕ./መስቀል /መስቀል




 እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!