መንፈሳዊ አገልግሎቶች

መንፈሳዊ አገልግሎቶች
    • የቄደር ጥምቀት አገልግሎት

    በሃይማኖት ዕዉቀት ማስፋፊያ ማህበር ዉስጥ በሳምንት
    አራት ቀን ማለትም ረቡዕ፣ ሐሙስ፣ አርብና ቅዳሜ
    ጠዋት ጠዋት በሰገነት ኪዳነምህረት የስብከተ ወንጌል
     አዳራሽ ዉስጥ ምክርና ትምህርት በመስጠት በሽተኞችና
     በተለያየ ሱስ ተይዘዉ የነበሩ በርካ ምዕመናን የቄደር ጥምቀት
     ተጠምቀዉ ከበሽታቸዉ ለመዳን ችለዋል እግዚአብሔር
     ይመስገን፡፡ አሁንም አገልግሎቱ እየተሰጠ በመሆኑ መጥተዉ ይጠመቁ!!!

    • የስብከተ ወንጌል አገልግሎት

    በሁሉም ክፍለ ሀገሮች በመዘዋወር ሞንታርቦ፣ ሰባኪና ዘማሪ
      በመያዝ የትራንስፖርት ነዳጅ ሙሉ ወጪዉን በመቻል በመላዉ
     ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ ሀገረ ስብከቶች በመሄድ የስብከተ ወንጌል
     አገልግሎት ለምዕመናን በነፃ እንዲማሩና እንዲያገኙ
      በመንቀሳቀሳችን ምእመናን የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙና
     ከኤች አይቪ ኤድስ በሽታ እራሳቸዉን እንዲጠብቁ የተያዙትም
    ንስሐ ገብተዉ ሥጋዉና ደሙ ተቀብለዉ እራሳቸዉን እንዲያጽናኑ
     አድርገናል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

    መንፈሳዉ ጉዞ

    ማህበራችን ምዕመናንን በማስተባበር ሀገርህንና ገዳምህን እወቅ
     ታሪክህን ጠብቅ በሚል መርህ መንፈሳዊ ጉዞ በማዘጋጀት
      የገጠር ቤተክርስቲያናትና ገዳማትን በመጎብኘት ምዕመናኑ
    በሄዱበት ቦታም እርዳ በመስጠት በርካታ የልማት
    ሥራዎችን ሰርተዉ ተመልሰዋል እግዚአብሔር ይመስገን፡፡


    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

    ለተጨማሪ  መረጃ
    ዌብሳይት  www.eotc-yemm.info.et