Sunday 29 September 2013

የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር የ28ተኛ ዓመት የወንጌል የምስረታ በዓሉን በታላቅ ድምቀት አከበረ


በወርሃ መስከረም በእለተ እሁድ የቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት ቀን ማለትም በ12/01/2006ዓ.ም የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር የ28ተኛ ዓመት የወንጌል የምስረታ በዓሉን በታላቅ ድምቀት አከበረ 

በእለቱ ፕሮግራሙን በጸሎት የከፈቱት  የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራችና የበላይ ጠባቂ እንዲሁም የጠቅላላ ጉባኤው አፈጉባኤ የሆኑት ሊቀ ትጉ.ባሕ ገ/መስቀል ኃ/መስቀል በአሉን አስመልክተው ንግግር ካደለጉ በኃላ ማህበሩ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ቀን ከለሊት ደፋ ቀና በማለት ለዚህ ላበቁት ለማህበሩ ደጋፊዎች መዕመናን ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል
 በመቀጠልም በዓሉን አስመልክተው ማኅበሩ ከዛሬ ጀምሮ በሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር ዘተዋህዶ በሚል በEBS TV ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 3፡30 እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ የሚተላለፍ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መጀመሩን ካበሰሩ በኃላ የ28ተኛ ዓመት የሚገልጽ ሻማ በመለኮስ ፕሮግራሙን በይፋ ከፍተዋል 



በመጨለሻም በአባታችን በሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ ኣባ ወልደማርቆስ  ቡራኬና ቃለምዕዳን ተሰጥቶ የዕለቱ ፕሮግራም ተፈፀመ
 


እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!